በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሁለት አይነት የአመራር ሂደቶች አሉ፡- ለውጥ-ተኮር (Transformational) እና ልውውጥ-ተኮር (Transactional)፡፡ የልውውጥ-ተኮር ስልት ጠቃሚነት እንደተጠበቀ ሆኖ ዘላቂውና ውጤታማው አመራር ለውጥ-ተኮሩ ነው፡፡
• ልውውጥ-ተኮር ስልት ተከታዮች ሊያገኙት ከሚችሉት ጥቅማ-ጥቅም አንጻር የማነሳሳት ስልት ነው፡፡•የትራንስፎርሜሽን ስልት ተከታዮች በራእዩ ስላመኑበት እንዲነሳሱ የማድረግ ብቃት ነው፡፡
• ልውውጥ-ተኮር ስልት ተከታዮች የተሰጣቸውን ተግባር እንዲፈጽሙና ከፈጸሙ የሚያገኙትን ጥቅም በማሳየት የተወሰነ ነው፡፡• የትራንስፎርሜሽን ስልት ተከታዮች ከሚጠበቅባቸው በላይ እንዲያከናውኑ የማነሳሳት ብቃት ያለው ስልት ነው፡፡
• ልውውጥ-ተኮር ስልት የዛሬው ተግባር የመፈጸሙና የመሳካቱ ጉዳይ ላይ ማተኮርና ለውጤቱም ምላሽ የመስጠት ጉዳይ ነው፡፡• የትራንስፎርሜሽን ስልት የነገን ራእይና ውጤት በማሰብ መነሳሳትና በመሪና በተመሪ መካከል የሚታይ የጋርዮሽ ጥረት ነው፡፡
• ልውውጥ-ተኮር ስልት ቅጥረኝነት፣ ለክፍያ መስራት፣ ከሚገኘው ጥቅም አንጻር ከፍና ዝቅ የሚል ትጋት ይታይበታል፡፡• የትራንስፎርሜሽን ስልት የራእይ ባለቤትነት፣ ቁጥጥርን የማይፈልግ ትጋት፣ ከክፍያ ያለፈ አጋርነት ይታይበታል፡፡
• ልውውጥ-ተኮር ስልት ስራ-ተኮር፣ ውጤት-ተኮር፣ ትርፍ-ተኮር፣ ሕግ-ተኮር ነው፡፡• የትራንስፎርሜሽን ስልት ሰው-ተኮር፣ አንድነት-ተኮር፣ አጋርነት ተኮር፣ ራእይ-ተኮር ነው፡፡
ከግል ሕይወት አንስቶ እስከ ድርጅትና ማሕበራዊ አመራር የሚዘልቀውን የዚህን ስልት እውነታዎች ለመገንዘብ መጽሐፉን አንብብ፡፡
call 0910717624
Call 0910458511
Bole Olympia
Kaleb
22 road infront of capita...
0900360167